النتائج (
الساندينيزية) 1:
[نسخ]نسخ!
ስልምልምታ ዝልፍልፍታ ጭልምልምታ
ብርቅርቅታ ውልብልብታ ብርቅርቅታ
ሕይወት
ፀፀት ፅታን ደርድራ
ምኞትን ከህልም አዋቅራ
በብቸኝነት ስታማቅቅ
ቀን ሌሊት አትል ስታስጨንቅ
ግን ህይወት
ብርቅርቅታ ናትና ታበራለች ቀን ጠብቃ
እንደጠለመች አትቀርም እንዳኮረፈች ተደብቃ
ዉሎ ቢያድርም ታበራለች በህብረ ቀለም አሸብርቃ
ሕይወት
እንደማለዳ ፀሐይ ብርሃን ስትፈጥቅ
እንደባህር አልማዝ ስትፍለቀለቅ
እንደእሳት ላንቃ አብረቅርቃ
ከቀትር ፀሐይ በርታ ደምቃ
ስትጀምር ማለት ድግዝግዝ
መባባት አይቀር መተከዝ
ሕይወት
ድቅዝቅዝታ ዝውርውርታ
ጥብርብርታ ጥንጥን በረቅ
ብልጭልጭታ ብርቅርቅታ
ከዳኒላ ስቲል ወደ አማርኛ ከተተረጎመው
ብርቅርቅታ መጽሐፍ የተወሰደ
يجري ترجمتها، يرجى الانتظار ..